ስጋበል
Appearance
- ለዕፅዋት፣ ስጋ በል ዕፅዋትን ይዩ።
ስጋበል በዘመናዊ ሥነ ሕይወት የጡት አጥቢ ክፍለመደብ ነው።
ከስጋበል ክፍለመደብ ውጭ ብዙ ሌሎች እንስሶች ደግሞ ስጋን ቢበሉም፣ እነዚህ ግን በተለይ ስጋን ለመብላት እንደ ተዘጋጁ ስለሚመስሉ ስለዚያው ነው «ስጋበል» የተባለ።
በክፍለመደቡ ውስጥ ዋና አስተኔዎች፦
- የአፍሪካ ዘምባባ ጥርኝ - አንድ ዝርያ
- የእስያ ሊንሳንግ - አንድ ወገን፣ ሁለት ዝርዮች
- የድመት አስተኔ - 15 ወገኖች፣ 41 ዝርዮች
- የጥርኝ አስተኔ - ጥርኝ፣ ሸለምጥማጥ ወዘተ. 15 ወገኖች፣ 34 ዝርዮች
- ዥብ - ሦስት ወገኖች፣ አራት ዝርያዎች
- የማዳጋስካር ፋሮ አስተኔ - 7 ወገኖች፣ 10 ዝርዮች
- ፋሮ - 14 ወገኖች፣ 33 ዝርዮች
- የውሻ አስተኔ 12 ወገኖች፣ 35 ዝርዮች
- ድብ - 5 ወገኖች፣ 8 ዝርያዎች
- ሞረስ - አንድ ዝርያ
- ባለ ጆሮ ባሕር አንበሣ - 7 ወገኖች፣ 15 ዝርዮች
- ጆሮ የለሽ ባሕር አንበሣ - 13 ወገኖች 18 ዝርዮች
- ቀይ ፓንዳ - አንድ ዝርያ፣ እስያ ብቻ
- የምጥማጥ አስተኔ - ከሸለምጥምጥ ሌላ፣ በአሜሪካዎችና በደቡብ-ምሥራቅ እስያ ብቻ የሚገኝ፣ 4 ወገኖች፣ 12 ዝርዮች
- የፋደት አስተኔ - 22 ወገኖች 57 ዝርዮች
- የራኩን አስተኔ - አሜሪካዎች ኗሪ፣ 6 ወገኖች፣ 14 ዝርያዎች
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |