1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሱዳን ግጭት በኢትዮጵያ የስደተኞችን ቀውስ አባብሷል

ሐሙስ፣ መስከረም 2 2017

በቅርቡ በቤኒሻንጉል የተከፈተው መጠለያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሱዳናዉያንን ያፈናቀለዉ የርስ በርስ ጦርነትን የሸሹ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች መኖሪያ ሆኗል። ከ50,000 በላይ ሱዳናዊያን ተፈናቃዮች ኢትዮጵያ ዉስጥ ተጠልለዋል። አትዮጵያ በአጠቃላይ አንድ ሚሊዮን ስደተኞችን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። 3.5 ሚሊዮን የዉስጥ ተፈናቃዮችም አልዋት።

https://p.dw.com/p/4kYY4
Afrika Äthiopien Flüchtlinge
ምስል Marco Simoncelli

የሱዳን ግጭት በኢትዮጵያ የስደተኞችን ቀውስ አባብሷል

በቅርቡ በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የተከፈተው የስደተኞች መጠለያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሱዳናዉያንን ያፈናቀለዉ አውዳሚ የርስ በርስ ጦርነትን የሸሹ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች መኖሪያ ሆኗል። በሱዳን የቀጠለዉ እና ባለፈዉ ዓመት በሚያዝያ ወር  በጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን በሚታዘዘው የሱዳን ጦር እና በብርጋዴየር ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ (ሔሜቲ) በሚመራው ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) መካከል የተቀሰቀሰዉ ግጭት በሲቢል ዜጎች ላይ ከፍተኛ ጥቃት እና ዉድመት በማድረሱ ሁለቱም ተቀናቃኝ ኃይሎች በጦር ወንጀል ተከሰዋል።

ከ50,000 በላይ ሱዳናዊያን ተፈናቃዮች ኢትዮጵያ ዉስጥ ተጠልለዋል። ሃገሪቱ ዉስጥ ከሚታየዉ አካባቢያዊ ቀዉሶች ጋር አትዮጵያ አንድ ሚሊዮን ስደተኞችን በማስተናገድላይ ትገኛለች።  የሱዳን ተፈናቃዮችን ተቀብላ ኢትዮጵያ እያስተናገደች ባለችበት በአሁኑ ወቅት በአፍሪቃ ቀንድ የሚገኙ ሃገራት የራሳቸዉን ችግር ለመፍታት እየጣሩ ነዉ። 

ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚታየዉ የምግብ እጥረት፤ በትግራይ በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች በሚታየዉ ግጭት  3.5 ሚሊዮን የ,ሃገር ዉስጥ ተፈናቃይ ህዝብንም ተጋፍጣለች። ታጣቂ ቡድኖች በሰብዓዊ ሠራተኞች ላይ በሚሰነዝሩት ቀጣይነት ባለዉ ጥቃት የእርዳታ ሰጭ ሰራተኞች ሥራ ተስተጓጉሏል።   

በክረምት ዝናብ መንገዶች በጭቃ የተዋጡበት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ግዛት አሶሳ አቅራቢያ የሚገኘዉ ኦዉራ መጠለያ ጣብያ በአሁኑ ወቅት 3,500 ተፈናቃዮች ይኖሩበታል። መጠለያዉ በመጪዎቹ ወራት ከ30,000 በላይ ተፈናቃዮችን ያስጠልላል ተብሎ ይጠበቃል።  

የክረምቱ ዝናብ እንዲያበቃ ከሚጠባበቁት መካከል የ32 ዓመቷ ሱዳናዊት ትሬዛ ዴንግ ቾል ትገኝበታለች።ቤኒሻንጉል በመሚገኘዉ መጠለያዉስጥ ከስድስት ልጆቿ ጋር የምትኖረዉ ትሬዛ፤ ካርቱምን ጥላ ወደ ጎረቤት ኢትዮጵያ የገባችዉ ባለፈዉ ዓመት ባለቤትዋ በጥይት ከተገደለ በኋላ ነበር።

«ባለቤቴን መቅበር እንኳ አልቻልኩም። ከዝያ ጎረቤቶቼ ለደኅንነታችን ገንዘብ ሰብስበው ከልጆቼ ጋር ከከተማው እንድሸሽ ሐሳብ አቀረቡልኝ» ስትል የምትናገረዉ ከካርቱም የተፈናቀለችዉ ሱዳናዊት፤ ስደትን ስትጀምር ነፍሰጡር የነበረች። ትሬዛ፤ በመጠለያ የአካባቢ ሰዎች እና የእርዳታ ድርጅቶች ሊረድዋት ሞክረዋል። ይሁንና ለልጆችዋ እና ለስዋ የሚሆን በቂ ምግብ እንደሌላት በተለይ በዝናብ ወቅት በጠባብ፣ ንጽሕና በጎደለው ሁኔታ ውስጥ እንደምትኖር ተናግራለች። ቴሬዛ በዝያዉ በመጠለያ ሻይ ለመሸጥ ሞክራም ነበር።

« ከአገሪ ስሸሽ ስልኬን ጠፋብኝ። በወቅቱ የረዱኝን ሰዎች ደዉዬ እንኳ ማግኘት አልቻልኩም። ፤ በህይወት ይኑሩ አይኑሩም አላዉቅም። ያሳላፍኩት ስናገር ቃላት ያጥረኛል። ባለቤቴን እወደዉ ነበር። አገሪን እወዳታለሁ፤ አሁን ብትወድምም መዉደዴን እቀጥላለሁ።»

በኢትዮጵያ ድንበር ላይ የሚገኘው እና ኩርሙክ የሚባለዉ፤ የስደተኞች መጠለያ ከእንጨት በተሠሩ ምሶሶዎች የተወጠሩት ነጫጭ ድንኳኖች በጭቃ ቆሽሽሸዉ ይታያሉ። ቦታዉ ከሱዳን ጦርነትን ሸሽተዉ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች መቀበያ እና መታወቅያ መስጫ ቦታ ነዉ።  እዚህ ቦታ ላይ የሚገኙት አብዛኞቹ ሱዳናዉያን የመጡት  ከደቡባዊ ብሉ ናይል ግዛት ሲሆን አንዳንዶች ግጭቱ ከተስፋፋበት ካርቱም እና ከዳርፉር  ከተሞች የመጡም አሉ።   

ትሬዛ ዴንግ ቾል በ2023 ከካርቱም ሸሽቶ የሸሸችው በግጭት ወቅት ባሏ በባዶ ጥይት ከተገደለ በኋላ ነበር
ትሬዛ ዴንግ ቾል በ2023 ከካርቱም ሸሽቶ የሸሸችው በግጭት ወቅት ባሏ በባዶ ጥይት ከተገደለ በኋላ ነበርምስል Marco Simoncelli

ስደተኞችን ለመርዳት ዋናዉ እና አሳሳቢዉ ጉዳይ የገንዘብ ድጋፍ መሆኑ ይታወቃል።  በተባበሩት መንግስታት እና በኢትዮጵያ ባለስልጣናት መሰረት የሰብአዊ ድጋፍ ጥረቶች  እየተደረገ አይደለም ሲሉ መግለፃቸዉ ተዘግቧል።    

የተባበሩት መንግሥታት የሰደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤን ኤች ሲ አር) ባለፈው ሚያዝያ ከሚያስፈልገው ግማሽ ያህሉን የገንዘብ ድጋፍ ጄኔቫ ላይ ከጋሾች ሰብስቧል። ይሁን እና አሁንም ችግሩ ሰፊ በመሆኑ ስደተኞች በየቀኑ ማግኘት ካለባቸዉ የእለት ጉርስ የሚያገኙት 60% ያነሰ ነው። የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ተመላሾች  አገልግሎት (RRS) ስደተኞች የሚያገኙት 25% ብቻ ነዉ ሲልም ገልጿል።

«የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ ቢሆንም፣ የተመደዉ በጀቱ ግን እየቀነሰ ነው። በአሁኑ ወቅት ስደተኞች ከዓለም ምግብ ድርጅት ብቻ ነዉ። ይህ ግን በቂ አይደለም። መጠለያዎቹ  ከአዲስ አበባ በጣም በራቀ እና ገጠራማ አካባቢዎች ስለሚገኙ በዝናብና በፀጥታ ስጋት ምክንያት በየወሩ መድረስ ያለበት ምግብ የሚደርሱት  ዘግይተዉ ነዉ።»

ማርኮ ሳይመንቼሊ / አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ