ውይይት:ሥነ ውበት
Appearance
ከላይ እንደገለፅኩት የአበቦችን የወፎችን ሥነ ዉበት ለመመልከት በዐይነ ህሊናችን ወደ አንድ ሰፊ የአበባ መስክ ከጥዋቱ ፩ ሰአት እስከ ፫ ወይም ከሰአት በኻላ ከ፲ እስከ ፲፪ ባለዉ ሰአት እንሂድ በደንብ አይነ ህሊናዎን ይክፈቱ··· አበቦችን ይመልከቱ የተለያየ ቀለማቸውን፣ቅርፃቸዉን ፤ ወፎችን ይመልከቱ የተለያየ ቀለማቸውን፣ቅርፃቸውን ፤ ወፎች አበቦችን እየቀሰሙ በተለያየ ዉብ ድምፅ ሲያቀነቅኑ ሲያፏጩ ሲያዜሙ ስናዳምጥ ሲደንሱ ስንመለከት ፤ አበቦች ፀጥታን ተላብሰዉ በወፎች ሙዚቃ የሚያዉደዉን ዉብ ጠረናቸዉን ከግራ ወደቀኝ በዉዝዋዜ እየነሰነሱ ዳንሳቸዉን ስንመለከት ፤ የዚህ ሁሉ ጥምር ሥነ ዉበት ይባላል።
ሔለን ደረሰ--2600:8806:2204:A800:A51B:CA20:1974:212B 23:29, 4 ሜይ 2016 (UTC) " የሰዉ ስነ ዉበት" ከላይ እንደ ገለፅኩት ስነ ዉበት ማለት እግዚያብሔር ፮ቱ ቀናቶች ዉስጥ የሰራቸዉ ዉብ የእጆቹ ስራዎች ስነ ዉበት ይባላል ብያለሁ፡፡ ከነዚህ ውበቶች ውስጥ ትልቁ እና አንደኛዉ የሰዉ ዉበት ነዉ፡፡ ምክንያቱም ሰዉ የእግዚያብሔር ሐምሣል ነዉ፡፡ የዚህ ሁሉ ዉብ ፍጥረት ባለቤት ዉቡ እግዚያብሔር ሰዉን በራሱ ዉበት ፈጠረ፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይም እንዲህ ይላል እግዚያብሔርም አለ:-ሰዉን በመልካችን እንደምሣሌያችን እንፍጠር ካለ በኧላ ሠዉን በመልኩ ፈጠረ፡፡ የሠወች ስነ ውበትም እንደ አበቦቹ የተለያየ የዉብት ቀለማቶች እና የዉብት ቅርፅና ፎርምች ባለቤቶች ናቸዉ፡፡