0% found this document useful (0 votes)
25 views6 pages

Check List For September 2017

Note

Uploaded by

biniyamb241
Copyright
© © All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as DOCX, PDF, TXT or read online on Scribd
0% found this document useful (0 votes)
25 views6 pages

Check List For September 2017

Note

Uploaded by

biniyamb241
Copyright
© © All Rights Reserved
We take content rights seriously. If you suspect this is your content, claim it here.
Available Formats
Download as DOCX, PDF, TXT or read online on Scribd
You are on page 1/ 6

በደብረ ብርሀን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ

/
ቅርንጫፍ ጽ ቤት

በቀጣይ አንድ ወር የሚከናወኑ ዋና ዋና

ስራዎች ቼክሊስት

መስከረም 03/2017 ዓ.ም

ደ/ብርሀን

መግቢያ፡-
የደብረ ብርሀን ከተማ በ 2016 በጀት ዓመት መጀመሪያ ከነበረዉ ሰፊ ስጋትና ፈተና አሁን ወዳለበት ተስፋ ሰጭ
መሻሻልና የለዉጥ ብርሃን ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የሆነዉና እየሆነ ያለዉ ደግሞ አመራሩ ከላይ እስከ ታች የሰላምና
የልማት ስራዉን ተናቦ እየገመመገመ በቁርጠኝነት ስለሰራና የተቀናጀ ድጋፍና ክትትል ስላደረገ ነዉ፡፡ አሁንም
ቢሆን ለዉጥ ማምጣትና ከችግራችን መላቀቅ የምንችለዉ የተጀመረዉን የሰላምና ጸጥታ ስራ በተጨማሪም ከሌሎች የልማት
ስራዎች ጋር ህዝብን ባሳተፈ መንገድ ስንመራና ቁርጠኝነትን ስንላበስ መሆኑ ግልጽ ነዉ፡፡

በተለይ የያዝነዉ አዲሱ የ 2017 መስከረም ወር በፊት ከነበሩብን ጥንካሬዎችና ድክመቶች ትምህርት ወስደን ለቀጣይ
የላቀ አፈጻጸም የምንዘጋጅበትና የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን የምናጠናቅቅበት ወቅት ነዉ፡፡ ይህንን ለማሳካት
ሀላፊነትን የሚወጣ የተደራጀና የተቀናጀ አመራር ያስፈልጋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የዞን አስተባባሪ ወደ ስልጠና
ስለገባ ዞን እንድናስተባብር ዉክልና የወሰድን አመራሮች ድርብ ሀላፊነት አለብን፡፡ ስለዚህ ሁላችንም አጠቃላይ
ተግባራትን በዉጤታማነት መምራት የሚጠበቅበት ሲሆን እንደ ከተማ ሁሉም ስራዎችን ከራሱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር
እያስተሳሰረ መምራት እንዲቻል የቀጣይ ወር ቼክሊስት ቀጥሎ ባለዉ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ተልኳል፡፡

 የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት


I. የፖለቲካና አደረጃጀት ስራዎችን አጠናክሮ መደገፍ

I.1 የተቋም ግንባታ ስራ አፈጻጸምን ማሳደግ፤


 እንደሚታወቀዉ በቅርቡ በከተማ መድረከ የ 2016 የእቅድ አፈጻጸም እና የ 2017 በጀት አመት እቅድ
ኦረንቴሽን ተካሂዶ እንደ ክፍለ ከተማ ሁሉም በሚባል ደረጀ የከተማዉን ሞዳሊቲ በመከተል የቀበሌ መዋቅርን
በመጥራት የእቅድ ግምገማና ኦረንቴሽን አካሂዷል፤
 በተመሳሳይ በርካታ ቀበሌወች ወደ ተግባር ገብተዉ አፈጻጸማቸዉን ገምግመዋል፤ እንዲሁም የቀጣይ አመት
እቅዳቸዉን የጋራ በማድረግ ለተግባራዊ ስራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡
 ሆኖም ከዚህ ጋር ተያይዞ አሁንም ቢሆን፡-
 በሁሉም ክፍለ ከተማ ደረጃ፤
 በሁሉም ቀበሌ ደረጃ፤
 በመሰረታዊ ድርጅት፣በህዋስ እና በአባል እቅድ ያላጠናቀቀ መዋቅርና አደረጃጀት ካለ በአህዛዊ
መረጃ ተመስርቶ ከወዲሁ ሁሉም እንዲያጠናቅቅ መደገፍና መከታተል ይጠይቃል፤
 በተመሳሳይ ከላይ በተጠቀሰዉ መዋቅርና አደረጃጀት እቅድ ሙሉ በሙሉ መታቀድ እንዳለበት ሆኖ በታቀደዉ
እቅድ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ወይም አረንቴሽን መስጠት አብሮ ተመጋግቦ መከናወን ያለበት ተግባር
ነዉ፡፡
 በየደረጃዉ ያሉ የድርጅት አደረጃጀቶች እግረ መንገዱን ያለባቸዉን የአመራር ክፍተት እንዲያሟሉና
መዋቅራቸዉን በአሰራሩ መሰረት እንዲያጠናክሩ ማስቻል፤
 በተለይ ታች በመሰረታዊ ድርጅትና በህዋስ ደረጃ ከሚካሄዱ የእቅድ ኦረንቴሽን መድረኮች ጎን ለጎን የፓርቲ
ተቋም ግንባታን ሊያጠናክሩ የሚችሉ ልዩ ልዩ የአሰራርና የአደረጃጀት መመሪያዎችን በማዉረድ የግንዛቤ ስራ
እንዲሰራና ተግባራት ሁሉ በተቀመጠላቸዉ የአሰራር ስርዓት እንዲከናወኑ ከወዲሁ ምቹ ሁኔታ መፍጠር፤
 የሁሉንም የፓርቲያችን ማህበራዊ መሰረቶች እንደ ተቋም ማጠናከርና ወደ ስራ ማስገባት፤
 የሚፈጠሩ የእቅድ ኦረንቴሽን መድረኮችን እና ሌሎች አጋጣሚዎችን በመጠቀም አዳዲስ እጩ አባላት እንዲፈሩ
መስራት፤
 የወጣትና ሴትሊግ አደረጃጀቶች በትይዩ የራሳቸዉን እቅድ አቅደዉ እንዲደግፉና መደበኛ ስራቸዉን
እንዲያጠናክሩ ማበረታት ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፤
1.2 የፖለቲካና አቅም ግንባታ ስራን ማጠናከር
 ማህበረሰቡን የሚያማርሩ የተለያዩ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ራሱን ህዝቡን ተሳታፊና አጋር በማድረግ
መከላከልና ህዝቡ ለሚፈጠሩ ችግሮች የባለቤትነት ስሜት ተሰምቶት አስፈላጊዉን እገዛ እንዲያደርግ
ማንቃት፤
 ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ ያለዉን የህዋስ መዋቅር ወቅታዊ አጀንዳ በመቅረጽ መደበኛ ዉይይቶች ሁሉን
ተደራሽ ባደረገ መንገድ እንዲካሄዱ ማድረግ፤
 ህዝቡ ባህሉንና እሴቱን ጠብቆ እንዲያጠናክርና በተለይ ለሰላሙና ለአካባቢዉ ደህንነት የባለቤትነት
ሚናዉን ማሳደግና በተመሳሳይ ወጣቱ ቀናዕይ የሆነ ግብረ-ገብነት እንዲላበስ የተለያዩ የግንዛቤ ስራዎችን
መስራት፤
 በየማህበራዊ መሰረቱ ያሉ አባላትን በማግኘት ለሰላም፣ልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ግንባር ቀደም
ሚናቸውን እንዲወጡ ፖለቲካዊ አቅም መፍጠርና የማነሳሳት ስራ መስራት።
 የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን አፈጻጸም ማጎልበት፡-
 የማህበራዊ ሚዲያ የተሳትፎን ማስፋት፤
 አዳዲስ ሀይል የሚያሰባስቡ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ማድረግ፤
 የሌላ አጀንዳ ከመከላከል ይልቅ አጀንዳ መስጠት ላይ ያተኮረ ስራ እንዲሰራ የህዝብ ግንኙነት
ባለሙያዎችን ማበረታታት፤
 በተለይ አመራሩ የማህበራዊ ሚዲያን ተሳትፎ እንዲያጠናክር ማነሳሳት፤
 ጥልቀትና ስፋት ያለው የተግባቦት ስራ በተከታታይነት መስራት፤
 የተመረጡና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን ባካተተ መንገድ ልዩ ልዩ መድረኮችን በመፍጠር የፖለቲካና
ህ/ግንኙነት ስራ እንዲሰራ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
II. በየአካባቢዉ የጸጥታ ስራን መከታተልና ሰላምን ማስፈን
 በአሁኑ ወቅት እንደ ከተማችን በአብዛኛዉ አካባቢ አንጻራዊ ሰላም ያለበት ቢሆንም አሁንም ቢሆን የህዝቡን
ነጻ እንቅስቃሴ የሚገቱና ሰላም የሚያሳጡ ተግባሮች ያሉ መሆኑ ግልጽ ነዉ፡፡
 ነገር ግን እስካሁን ድረስ በተሰራ ሰፊ ስራ በርካታ ለዉጦች ቢመዘገቡም ሰላሙን የበለጠ በማጉላትና ህዝቡ
ሙሉ ነጻነት ተሰምቶት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተግባሩን በሙሉ አቅሙና ፍላጎቱ እንዲሰራ በማድረግ በኩል
የሚቀር ሰፊ ስራ ስላለ ሁላችንም በቀጣይ አንድ ወር ዉስጥ ቀጥሎ ያሉትን ነጥቦች ታሳቢ አድርገን መስራትና
ማስተባበር ይኖርብናል፤
 በየአካባቢዉ ስጋትና ተጋላጭነትን ለይቶ የጸጥታና የፖለቲካ አመራር ስምሪት መስጠት፤
 ከመከላከያና ከሌሎች የጸጥታ አመራሮች ጋር ተናቦና ተቀናጅቶ መስራት፤
 ዋና ዋና የከተማ መግቢያና መዉጫ በሮች ላይ ጥብቅ ጥበቃና ፍተሻ እንዲከናወን መስራትና ማስተባበር፤
 የመረጃ ስርዓታችን በማጠናከር ታማኝ፣ፈጣን እና ሁሉንም አካባቢ እንዲሸፍን በትኩረት መስራት፤
 በቀጣይ የሚከበረዉን የመስቀል በአል አስመልክቶ ከወዲሁ የሰላምና ደህንነት ቅድመ ዝግጅት ማድረግና
በዓሉ በሁሉም የከተማችን አካባቢዎች በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ በቂ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
 ከዚሁ የመስቀል በዓል ጋር በተያያዘ የአካባቢ አቅምን ተጠቅሞ ሀብት በማሰባሰብ ስምሪት ላይ ላለዉ
የጸጥታ መዋቅር የበዓል መዋያ ድጋፍ በማሰባሰብ ማበረታታት፤
 በተወሰነ መልኩም ቢሆን ቀበሌዎች የተጀመሩትን የብሎክ አደረጃጀቶች በማጠናከር የእገታ፣ስርቆትና
ሌሎች ወንጀሎችን መቆጣጠር፤
III. የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች አፈጻጸምን መከታተል

3.1. የልማት ስራዎችን መደገፍና መከታተል


 የተጀመረውን አንጻራዊ ሰላም ሙሉ ማድረግና ማጽናት የሚቻለው የአቀድናቸውን የልማትና መልካም
አስተዳደር ስራዎች በመፈጸም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ሲቻል ነው፤
 ስለሆነም፡- በሁሉም ተቋማት የታቀዱ ዋና ዋና ስራዎችን ከሰላሙ ስራ ጋር አቀናጅቶና በስራ ክፍፍል
እየገመገሙ መምራትና መፈጸም ይገባል፡፡ በዚህም የከተማዉን ልማት ማሳለጥና ኢኮኖሚወን ማነቃቃት
የሚያስችሉ ስራዎችን መስራት ይገባል፡፡
 የትምህርት ዘርፉን በጥብቅ ዲሲኘሊን በመከታተል የመማር ማስተማሩ ስራ ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል
ከወዲሁ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር መረባረብ፤
 በሌላ በኩል ወደ ትምህርት ቤት ያልመጡ ህፃናት የመማር መብታቸው እንዲከበር ከማህበረሰቡ ጋር
በመመካከር በአለዉ አጭር ጊዜ ወደ ትምህርት ገበታቸዉ እንዲመለሱ በተግባር የሚታይ ስራ መስራት፤
 በማሳተፍ የትምህርት ተቋሙን መደገፍ፤
 የትምህርት ምዝገባ ሽፋንን ማስፋትና ማጠናቀቅ፤
 መምህራን ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግና በየትምህርት ቤቱ የገባና ያልገባዉ እየተለየ ተጠያቂነት
እንዲሰፍን ማድረግ፤
 ትምህርት የጀመሩ ትምህርት ቤቶችን መለየት/እንደ ከተማ አስተዳደር ያለ የመንግስት ትምህርት ቤት
ብዛት…….እስካሁን ወደ ተግባር የገባ……..? በሚል እስከ ታች በዚህ ቅኝት መከታተል፤
 የስራ እድል ፈጠራንን በተመለከተ ከወዲሁ የጠራ እቅድ እንዲታቀድ መደገፍና ወደ ስራ ማስገባት፤
 የበጀት ዓመቱን የመደበኛ ገቢ እቅድን በማወቅ በየዕለቱ ያለዉን የገቢ አፈጻጸም ለዉጥ መከታተልና
የላቀ እድገት እንዲመዘገብ መስራት፤
 ኢኮኖሚያዊ ህገ-ወጥነትን መቆጣጠርና በዘርፉ የሚታይ ግድፈትን ፈጥኖ ማረም፤
 በተለይ በከተሞች የግብዓት አቅርቦት እንዲሻሻል ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በጋራ መስራት፤
 እቅድን ታሳቢ ባደረገ መንገድ የፓርቲ ገቢ አፈጻጸምን በሁሉም ማህበራዊ መሰረት ማሳደግ፤
 ካሁን በፊት በከተማ የተሰራጨዉን የልሳነ-ብልጽግና መጽሄት ገቢን ፈጥኖ መዝጋት፤
3.2. የመልካም አስተዳደር ስርዓት እንዲሻሻል መስራት
 ከከተማ ጀምሮ የተጀመሩ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ መድረኮችን ተደራሽነታቸዉን
እስከ ቀበሌ ማድረስና ጥራታቸዉን ማስፋት፤
 በየመዋቅሩ የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ማጎልበትና በዘርፉ ያሚታዩ ዉስንነቶችን በአግባቡ ለይቶ
ማሻሻል፤
 በሚፈጠሩ የመልካም አስተዳደር መድረኮች ሁሉ በተለይ የአገልጋይነት እይታችን እና ተግባራዊ ምላሽ
ላይ ያለዉን ችግር ማስተካከል፤
 በየደረጃው የሚገኙ የተቋም ኃላፊዎችና ባለሞያዎች በተቋማቸዉ ተገንተው ባለጉዳይን ዘላቂ በሆነ
አግባብ በቀናነት እንዲያስተናግዱ ማድረግ፤
 በየዘርፉ ያለዉ ባለሙያ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከስራ ገበታዉ ዉጭ እንዳይሆንና በተቋሙ ተገንቶ
የሚጠበቅበትን አገልግሎት እንዲሰጥ ማስቻልና አስፈላጊ ከሆነም በሱፐርቪዥን በመቃኘት ክፍተት
ያለበትን ለይቶ መገምገም፤

IV. የድጋፍና የአፈጻጸም አቅጣጫዎች


 በከተማ የተወከለዉ አመራርና ወደ ስልጠና ያልገባዉ አስፈጻሚ አመራር አመራሩን በተመረጡ ዋና ዋና ስራዎች
ስምሪት መስጠትና ወቅቱን የጠበቀ የተግባርና የተልዕኮ ግምገማ ማካሄድ፤
 በተደራጀ ሁኔታ ከዞን እስከ ቀበሌ ተግባርን፣መዋቅርንና ዘርፍን ተከፋፍሎ መምራት፤
 አጠቃላይ ከተማዉን የሚያስተባብሩ አመራሮች ከጸጥታ ሚኒ ካቢኔዉ ጋር የሰላምና ጸጥታ ስራዉን እየገመገሙ
በአግባቡ መምራት፤
 ከከተማ እስከ ቀበሌ ድረስ የሚገጥሙ ችግሮች ካሉ በሚደርስ መረጃ መሰረት ፈጣን የሆነ ምላሽ መስጠትና
መፍትሄ አፈላላጊ መሆን፤
 ከከተማ እስከ ቀበሌ ድረስ ሌላዉን የሚጠቅም ተሞክሮ ካለ በአጭሩ ቀምሮ ማስተላለፍ፤
 መደበኛ የአመራርና አደረጃጀት ኮሚቴ ግምገማና ዉይይቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል፤
 ልዩ ልዩ የፖለቲካና የአደረጃጀት ስራዎችን እንደየ ባህሪያቸዉ አቅም ያላቸዉን አመራሮች በማሰማራት
መምራት፤
 የከ/አስተዳደር አመራሩን በመደበኛና ወቅታዊ ስራዎች በተለያዩ አማራጮች አግኝቶ መገምገምና ለቀጣይ ስራ
ማሰማራት፤
 የክ/ከተማና ቀበሌ አመራሩን በአካል ጭምር ወርዶ ማግኘትና አቅም የሚሆን ችግር ፈች አቅጣጫ መስጠት፤
V. በየደረጃዉ የሚደረግ የሪፖርት ግንኙነት በተመለከተ
 በየቀኑ ከቀበሌ እስከ ከተማ ደረጃዉን ጠብቆ የስልክና አጫጭር የጽሁፍ የሪፖርት ግንኙነት ይኖራል፡፡
 ለዚህ የሚሆን የመረጃና የሪፖርት ቡድን በየደረጃዉ ማዘጋጀት፤
 ከከተማ እስከ ቀበሌ ድረስ የሪፖርት አፈጻጸምን እንዲሁም ድጋፍና ክትትልን መሰረት በማድረግ ግብረ-መልስ
ይሰጣል፤
 በአጠቃላይ ተከታታይነት ያለዉና ወደ ስራ የሚያስገባ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም ቼክሊስቱን
እና የአካቢን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ዉስጥ ባስገባ ስልት አመራሩ እና መላ መዋቅሩ ጊዜዉን በሙሉ ዉጤታማ ስራ
ላይ እንዲያዉል ማስቻል ከሁላችንም የሚጠበቅ ተግባር ነዉ፡፡

You might also like