Jump to content

ፍሩት ኬክ

ከውክፔዲያ

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
5 የሾርባ ማንኪያ (125 ግራም) የገበታ ቅቤ
1 የቡና ስኒ (100 ግራም) ስኳር
4 የቡና ስኒ (200 ግራም) የፉርኖ ዱቄት
3 ዕንቁላል
1 የሾርባ ማንኪያ ቤኪንግ ፓውደር
1 የቡና ስኒ (100 ግራም) ዘቢብ
ግማሽ የቡና ስኒ (50 ግራም) የተገረደፈ ኦቾሎኒ
1 የሾርባ ማንኪያ ተከትፎ የደረቀ የብርቱካን ልጣጭ
1. ቅቤውንና ስኳሩን በደንብ እስኪለሰልስ ድረስ በዕንቁላል መምቻ መምታት፤
2. ዕንቁላሉን ለብቻው መምታት፤
3. ዕንቁላሉን ውሁዱ ላይ እየጨመሩ ኩፍ እስኪል መምታት፤
4. ዱቄትና ቤኪንግ ፓውደሩን ለብቻ ቀላቅሎ ወደ ውሁዱ ጨምሮ በእጅ ወይም በዝርግ ጭልፋ ማዋሃድ፤
5. ኦቾሎኒውን፣ ዘቢቡንና የብርቱካን ልጣጩን መጨመር፤
6. በዘይት የተቀባ የኬክ መጋገሪያ ትሪ ላይ ሊጡን በማድረግ የሞቀ የዳቦ መጋገሪያ ውስጥ ማብሰል (በ170 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ለአንድ ሰዓት ያክል ማቆየት)፤
7. ሲቀዘቅዝ ማቅረብ፡፡