Tenor የTenor ሞባይል መተግበሪያን፣ በhttp://tenor.com ላይ የሚገኘውን የTenor ድር ጣቢያን፣ የTenor ቅጥያዎችን እና የTenor ኤፒአይን ያካትታል። የTenor ኤፒአይ ከሶስተኛ ወገን መሣሪያዎች ወይም አገልግሎቶች ጋር ሊዋሃድ ይችላል፣ ነገር ግን ከTenor ጋር የሚዛመዱ ማናቸውም አገልግሎቶች የሚቀርቡት በGoogle ነው።
Tenorን ለመጠቀም፣ (1) የGoogle አገልግሎት ውል እና (2) ይህን የTenor ተጨማሪ የአገልግሎት ውል («የTenor ተጨማሪ ደንቦች») መቀበል አለብዎት።
እባክዎ እያንዳንዱን እነዚህን ሰነዶች በጥንቃቄ ያንብቡ። እነዚህ ሰነዶች በአንድ ላይ «ደንቦች» በመባል ይታወቃሉ። አገልግሎቶቻችንን ሲጠቀሙ ከእኛ የሚጠብቁትን እና ከእርስዎ የምንጠብቀውን ይመሰርታሉ።
እነዚህ የTenor ተጨማሪ ደንቦች ከየGoogle አገልግሎት ውል ጋር የሚጋጩ ከሆነ እነዚህ ተጨማሪ ደንቦች ለTenor ይገዛሉ።
ምንም እንኳ የእነዚህ ደንቦች አካል ባይሆንም እንዴት የእርስዎን መረጃ ማዘመን፣ ማስተዳደር፣ ወደ ውጭ መላክ እና መሰረዝ እንደሚችሉ በተሻለ እንዲረዱ የእኛንየግላዊነት መመሪያ እንዲያነብቡ እናበረታታዎታለን።
Tenor ይዘትዎን እንዲያስገቡ፣ እንዲያከማቹ፣ እንዲልኩ፣ እንዲቀበሉ ወይም እንዲያጋሩ ያስችልዎታል። የእርስዎ ይዘት በGoogle አገልግሎት ውል ውስጥ በተገለጸው መሠረት ለGoogle ፈቃድ ተሰጥቶታል — ስለዚህ ይዘትን ወደ Tenor ከሰቀሉ ይህን ይዘት ለተጠቃሚዎች ማሳየት እና ሲመራን ማጋራት እንችላለን፣ እንዲሁም እነዚህ ተጠቃሚዎች (በTenor ኤፒአይ በኩል ይዘት የሚደርሱ ተጠቃሚዎችን ጨምሮ) ይህን ይዘት ማየት፣ ማጋራት እና መቀየር ይችላሉ።
2. የተከለከለ ይዘት።
2.1 Tenorን ለማንኛውም የንግድ ዓላማ ወይም ለማንኛውም የሶስተኛ ወገን ጥቅም መጠቀም የለብዎትም።
2.2 በGoogle አገልግሎት ውል ላይ እንደምናብራራው ለሁሉም ሰው የተከበረ አካባቢን መጠበቅ እንፈልጋለን። Tenorን በሚጠቀሙበት ጊዜ የእኛን የፕሮግራም መመሪያዎች እና በGoogle የአገልግሎት ውል ውስጥ የተገለጹትን የመሠረታዊ ስነ ምግባር ደንቦች መከተል አለብዎት። በተለይ Tenorን ሲጠቀሙ የሚከተሉትን ማድረግ የለብዎትም፡-
ሀ. የሚከተሉትን የሚያደርግ ማንኛውንም ይዘት ማስገባት፣ ማከማቸት፣ መላክ ወይም ማጋራት፦
፩. የሌላ ሰው የአእምሯዊ ንብረት መብቶች፣ ወይም የይፋዊነት መብቶች ወይም ግላዊነትን የሚጥስ ወይም ያለአግባብ የሚጠቀም ጨምሮ የሚመለከተውን ህግ ወይም የሌሎች መብቶችን መጣስ፣ ወይም የሚጥስ ማንኛውንም ምግባር ማበረታታት፤
፪. በቅድሚያ የተሰጠ ፈቀዳ ሳይኖር ስለሌላ ማንኛውም ሰው የግል ወይም የእውቂያ መረጃን መያዝ፤
፫. ሕገ-ወጥ ወይም ጎጂ እንቅስቃሴዎችን ወይም ነገሮችን ማስተዋወቅ፤
፬. አጭበርባሪ፣ አሳሳች ወይም አታላይ መሆን፤
፭. ውሸት ወይም ስም አጥፊ መሆን፤
፮. አጸያፍ ወይም የወሲብ ስራ መሆን፤
፯. በማንኛውም ግለሰብ ወይም ቡድን ላይ አድልዎ፣ ጭፍን ጥላቻ፣ ዘረኝነት፣ ጥላቻ፣ ትንኮሳ ወይም ጉዳት ማበረታታት ወይም መመስረት፤
፰. ሃይለኛ ወይም የሚያስፈራራ ወይም ማንኛውንም ግለሰብ፣ ቡድን ወይም ድርጅት የሚያሰጋ ሁከትን ወይም ድርጊቶችን ማስተዋወቅ፤ ወይም
ለ. ኢሜይል፣ ደብዳቤ፣ አይፈለጌ መልዕክት፣ ሰንሰለት ደብዳቤዎች ወይም ሌሎች መጠይቆችን ጨምሮ ማንኛውንም ያልተጠየቀ ወይም ያልተፈቀደ ማስታወቂያ፣ የማስተዋወቂያ ቁሳቁሶች ወይም ግንኙነቶች መላክ።