Jump to content

ነሐሴ ፲፫

ከውክፔዲያ
The printable version is no longer supported and may have rendering errors. Please update your browser bookmarks and please use the default browser print function instead.

ነሐሴ ፲፫ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፵፫ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፳፫ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፳፪ ቀናት ይቀራሉ።


ከኢትዮጵያን ሪፖርተር ፦ "ሆያ ሆዬ" በሚል አርስት ነሐሴ ፲፫ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም የወጣ አንቀጽ

"መጣና ባመቱ አረ እንደምን ሰነበቱ ክፈትልኝ በሩን የጌታዬን ሆያ-ሆዬ-ሆ"

እያሉ ልጆች በዜማ እያወረዱ፣ በየመንደሩ እየተሽከረከሩ የሚጫወቱት ለቡሄ በዓላቸው ነው፡፡ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የኖረ፣ አሁንም እየቀጠለ ያለ ትውፊት ነው፡፡

ዛሬ ነሐሴ ፲፫ ቀን የበዓሉ ክብር ነው፡፡ በተለይ ነባሩን ትውፊት ይዞ የሚገኘው በገጠር አካባቢ ነው፡፡ ቡሄኞቹ ልጆች ለበዓሉ አስቀድመው ይዘጋጃሉ፡፡ ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮሁ ይሰነብታሉ፡፡ እናቶችም ለበዓሉ የሚሆን ሙልሙል ዳቦ ያዘጋጃሉ፡፡ እየጨፈሩ ለሚመጡ ልጆችም ያበረክታሉ፡፡

አዲስ አበባ ባሁን ጊዜ እየዞሩ ከሚጨፍሩት ሕፃናት ሌላ በከተማዋ ዳርቻ የሚኖሩ ጎረምሶችም በኦሮምኛ የቡሄ ጭፈራቸውን፣ ቄጠማ እያበረከቱ የሚያስኬዱበት ሥርዓት አላቸው፡፡

ቡሄ ጎላጣ፣ መላጣ ማለት እንደሆነ መጻሕፍት ይገልጻሉ፡፡ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ የሚታይበት እንደሆነ ይታመንበታል፡፡

ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት ስለማይኖርም "ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፣ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት" እየተባለም ይነገራል፡፡

ለባህላዊው በዓል መሠረት የሆነው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚያስተምርበት ጊዜ በታቦር ተራራ ላይ (ደብረ ታቦር) ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን የገለጠበት ዕለት እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡


ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች

  • ፲፱፻፹፱ ዓ/ም በደብረ ዳሞ ገዳም ብዙ ታሪካዊ ፤ ሃይማኖታዊ እና ምሥጢራዊ የመጽሐፍ ቅርሶችን ያካተተው ቤተ መጻሕፍትና ሃይማኖታዊ 'ንዋየ ቅድሳት' የተከተቱበት ግምጃ ቤት ባልታወቀ ምክንያት በእሳት አደጋ ቃጠሎ ወደሙ።[1]

ልደት

ዕለተ ሞት

ዋቢ ምንጮች

  1. ^ ለይኩን ብርሃኑ ፥ "ለምንት አንገለጉ አሕዛብ" (ጥቅምት 1997)፥ ገጽ 15


የኢትዮጵያ ወራት
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ