Jump to content

ከ«ኔዘርላንድ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

ከውክፔዲያ
Content deleted Content added
መስመር፡ 36፦ መስመር፡ 36፦
በሆላንድ ገና፣ የክርስቶስ ልደት፣ በተለመደው ቀን ይከበራል፣ [[ቅዱስ ኒኮላስ]] ግን ([[ሳንታ ክሎዝ]] ወይም በሆላንድኛ /ስንተርክላስ/) የሚከበርበት ቀን በኅዳር 25 ወይም ከገና በፊት አንድ ወር ያህል ነው።
በሆላንድ ገና፣ የክርስቶስ ልደት፣ በተለመደው ቀን ይከበራል፣ [[ቅዱስ ኒኮላስ]] ግን ([[ሳንታ ክሎዝ]] ወይም በሆላንድኛ /ስንተርክላስ/) የሚከበርበት ቀን በኅዳር 25 ወይም ከገና በፊት አንድ ወር ያህል ነው።


አራስ ልጅ ለሚጎበኙ ሰዎች [[ብስኩት]]ና የ[[እንሶስላ]] ዘር በስኳር ማቅረብ ሌላ የሆላንድ ባህላዊ ልማድ ነው። ለ[[ፋሲካ]] በዓል ደመራዎች ይነደዳሉ፣ የንጉሥ ልደት ቀን በሚያዝያ ፲፱ ሲከበር፣ ነጋዴዎች ብርቱካን ልብስ ለብሰው በከተሞች መሃል ገበያ ያደርጋሉ።
አራስ ልጅ ለሚጎበኙ ሰዎች [[ብስኩት]]ና የ[[እንሶስላ]] ዘር በስኳር ማቅረብ ሌላ የሆላንድ ባህላዊ ልማድ ነው። ለ[[ፋሲካ]] በዓል ደመራዎች ይነደዳሉ፣ የንጉሥ ልደት ቀን በሚያዝያ ፲፱ ቀን ሲከበር፣ ነጋዴዎች ብርቱካን ልብስ ለብሰው በከተሞች መሃል ገበያ ያደርጋሉ።


{{በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ አገሮች}}
{{በአውሮፓ ውስጥ የሚገኙ አገሮች}}

እትም በ11:08, 19 ጁላይ 2017

Koninkrijk der Nederlanden
የሆላንድ መንግሥት

የሆላንድ ሰንደቅ ዓላማ የሆላንድ አርማ
ሰንደቅ ዓላማ አርማ
የሆላንድመገኛ
የሆላንድመገኛ
ዋና ከተማ አምስተርዳም
ብሔራዊ ቋንቋዎች ሆላንድኛ
መንግሥት
{{{ንጉሥ
ጠቅላይ ሚኒስትር
 
ቪለም-አለክሳንደር
ማርክ ሩተ
የመሬት ስፋት
አጠቃላይ (ካሬ ኪ.ሜ.)
 
41,526 (134ኛ)
ገንዘብ ዩሮ
ሰዓት ክልል UTC +1
የስልክ መግቢያ +31


ሆላንድ (ወይም ኔዘርላንድ ኔዘርላንድስ ኔደርላንድሆላንድኛNederland /ነድርላንት/) በአውሮጳ ውስጥ የሚገኝ አገር ነው።

ስም

ኔዘርላንድ ብዙ ጊዜ «ሆላንድ» ሲባል፣ ይኸው ስያሜ በትክክል ግን የአንዱ ትልቅ ክፍላገር ስም ብቻ ነው። በሆላንድኛ፣ የ«ነድርላንት» ትርጒም «ታችኛ አገር» ሲሆን በብዙዎች ቋንቋዎች ያለው ስም ከዚህ ነው። የ«ሆላንድ» ትርጒም ደግሞ ከጥንታዊ ሆላንድኛ «ሆልት-ላንት» ማለት «እንጨት አገር» መጣ።

ባህል

የሥራ ቋንቋ ሆላንድኛምዕራብ ጀርመናዊ ቋንቋዎች መካከል ይቆጠራል፤ እንዲሁም በግዛቱ ውስጥ የሚነገረው ሌላ ቋንቋ ፍሪዝኛ በቅርብ ይዛመዳል።

በሆላንድ ብዙ መስኖ፣ ቦይ ይታያል፣ ሕዝባዊ መጓጓዣ አገልግሎቱ ማለፊያ ነው። ብዙ ሕዝብ በብስክሌት ይጓዛሉ፣ ብዙ ጊዜም ይዘንባል። ብዙ ሰዎች በቡና ሱቅ ፊት ትቀምጠው ቡና ሲጠጡ ይታያሉ። ልማዳዊ አበሳሰሉ በጣም የተቀመመ አይደለም። ብዙ ታዋቂ አይቦች (ፍሮማጆ) ለምሳሌ ጉዳ ፍሮማጆ፣ ከኔዘርላንድ አሉ።

ሁለት በዓለም ዝነኛ የሆኑ የሆላንድ ሰዎች ሬምብራንት፣ የ17ኛው ክፍለ ዘመን ሰዓሊ፣ እና ቪንሰንት ቫን ጎ፣ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ሰዓሊ፣ ናቸው። 1600ዎቹ የኔዘርላንድ ወርቃማ ዘመን ተብሏል።

ክሪኬት የተባለው የኳስ ጨዋታ ደግሞ በሆላንድ እንደሚወድድ እንደሚጫወትም በተረፈው ዓለም ብዙ ጊዜ አይታስብም። በመላው አገር የክሪኬት ቡድኖችና ብሔራዊ አሸናፊነት ውድድር አላቸው። ሆኖም እግር ኳስ፣ ፈጣን ተሽካካሪ ጫማ ስፖርት፣ እና ሆኪ (ገና የመሰለ ጨዋታ) ደግሞ ዋና ተወዳጅ መሠረት አላቸው።

በሆላንድ ገና፣ የክርስቶስ ልደት፣ በተለመደው ቀን ይከበራል፣ ቅዱስ ኒኮላስ ግን (ሳንታ ክሎዝ ወይም በሆላንድኛ /ስንተርክላስ/) የሚከበርበት ቀን በኅዳር 25 ወይም ከገና በፊት አንድ ወር ያህል ነው።

አራስ ልጅ ለሚጎበኙ ሰዎች ብስኩትና የእንሶስላ ዘር በስኳር ማቅረብ ሌላ የሆላንድ ባህላዊ ልማድ ነው። ለፋሲካ በዓል ደመራዎች ይነደዳሉ፣ የንጉሥ ልደት ቀን በሚያዝያ ፲፱ ቀን ሲከበር፣ ነጋዴዎች ብርቱካን ልብስ ለብሰው በከተሞች መሃል ገበያ ያደርጋሉ።